የቅዱሳን በዓላት አፕሊኬሽን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዕለቱ ታስበው የሚውሉትን ቀናት
ዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ እነዚህም ቀናት በስንክሳር ላይ ሰፍረው የሚገኙት እና አብዛኛው ሰው በተለምዶ
ከሚያውቃቸው ቀናት በተጨማሪ ያሉ ቀናትን ይይዛል። በየዕልቱ እንዲሁም በየወሩ ታስበው የሚውሉ ቀናት
ይለያያሉ፤ ማለትም ፥ ጥቅምት አንድ እና ህዳር አንድ ዕለት ተመሳሳይ በዓል አይደለም ከልደታ ለማርያም
በስተቀር። በዚህ መሰረት ይህ አፕልኬሽን በዓመቱ ውስጥ ያሉትን የእያንዳንዱን ዕለታት ዝርዝር የያዘ ሲሆን፤
በየቀኑም ማስታወሻ (Notification) አለው።
